ስለ ኢትዮ ሳት ሙሉ መረጃ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ኡመር ዲሽ ነኝ ➲ ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስለ ETHIOSAT ከሚነሱ ጥያቄዎች መካካል ግልፅ መረጃ እንዲኖራቹ የሚከተሉትን ነገሮች አዘጋጅተናል።


⓵ ኢትዮሳት ከተቀላቀሉ የሀገር ውስጥ ቻናሎች አብዛኞቹ ከ ታህስስ 22 ጀምሮ የ ናይል ሳት ስርጭታቸው ያቆማል።


⓶ ኢትዮሳት ለመጠቀም የግድ ሰሀኑ አቅጣጫ ከነበረበት በተቃራኒ በስተምስራቅ ዞሮ መስተካከል ይኖርበታል


⓷ ኢትዮሳት ላይ የገቡ ቻናሎች አብዛኞቹ በHD ስርጭት ስለሚተላለፉ አነርሱን ለማግኘት HD ሪሴቨር ያስፈልጋል።


⓸ ኢትዮሳት በ SD ይሰራል!   ነገር ግን እስካሁን ባለው ሁኔታ በ Sd ሪሴቨር የሚሰሩት ውስን(14) ታናሎች ብቻ ናቸው።


⓹ ኢትዮሳት እና ናይል ሳት በ አንድ ሰሀን አይሰሩም ሁለቱንም ለመጠቀም ሁለት ሰሀን ያስፈልጋል።


⓺ ኢትዮ ሳት የሚገኝበት ሳተላይት NSS 12 57E ሙሉ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሽፋን ስላለው ከ 60CM ዲሽ ጀምሮ ይሰራል።


⓻ ሪሴቨሮች ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል በተለይ SUPERMAX 2350 SUPERTECH

 በ 11105 H  45000 ላይ ሲግናል ችግር ያመጣል መፍትሄው መቀየር ነው።


👉 ይህ frequency 11105 H 45000 የገመድ ችግር ካለም የማስቸገር ባህሪ አለው


⓼ ሪሴቨራቹ ላይ NSS12 የሚል ከሌለ SATTELITE LIST ላይ ADD ማድረግ ወይም አንደኛው ሳተላይት ላይ ፍሪክዌንሲውን መሙላት ይቻላላል።


✅  ሌሎች ያላችሁን ጥያቄዎች በ Comment Box ላይ ብቻ አቅርቡ።

Comments