ስለ ኢትዮ ሳት ሙሉ መረጃ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ኡመር ዲሽ ነኝ ➲ ሰሞኑን በተደጋጋሚ ስለ ETHIOSAT ከሚነሱ ጥያቄዎች መካካል ግልፅ መረጃ እንዲኖራቹ የሚከተሉትን ነገሮች አዘጋጅተናል። ⓵ ኢትዮሳት ከተቀላቀሉ የሀገር ውስጥ ቻናሎች አብዛኞቹ ከ ታህስስ 22 ጀምሮ የ ናይል ሳት ስርጭታቸው ያቆማል። ⓶ ኢትዮሳት ለመጠቀም የግድ ሰሀኑ አቅጣጫ ከነበረበት በተቃራኒ በስተምስራቅ ዞሮ መስተካከል ይኖርበታል ⓷ ኢትዮሳት ላይ የገቡ ቻናሎች አብዛኞቹ በHD ስርጭት ስለሚተላለፉ አነርሱን ለማግኘት HD ሪሴቨር ያስፈልጋል። ⓸ ኢትዮሳት በ SD ይሰራል! ነገር ግን እስካሁን ባለው ሁኔታ በ Sd ሪሴቨር የሚሰሩት ውስን(14) ታናሎች ብቻ ናቸው። ⓹ ኢትዮሳት እና ናይል ሳት በ አንድ ሰሀን አይሰሩም ሁለቱንም ለመጠቀም ሁለት ሰሀን ያስፈልጋል። ⓺ ኢትዮ ሳት የሚገኝበት ሳተላይት NSS 12 57E ሙሉ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሽፋን ስላለው ከ 60CM ዲሽ ጀምሮ ይሰራል። ⓻ ሪሴቨሮች ላይ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል በተለይ SUPERMAX 2350 SUPERTECH በ 11105 H 45000 ላይ ሲግናል ችግር ያመጣል መፍትሄው መቀየር ነው። 👉 ይህ frequency 11105 H 45000 የገመድ ችግር ካለም የማስቸገር ባህሪ አለው ⓼ ሪሴቨራቹ ላይ NSS12 የሚል ከሌለ SATTELITE LIST ላይ ADD ማድረግ ወይም አንደኛው ሳተላይት ላይ ፍሪክዌንሲውን መሙላት ይቻላላል። ✅ ሌሎች ያላችሁን ጥያቄዎች በ Comment Box ላይ ብቻ አቅርቡ።